በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት 7.1 ቢሊየን ብር ትርፍ ማግኘት ችለናል – የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልተቋሙ ወጪዎችን በመቀነስና የገቢ አማራጮቹን በማስፋት ከዚህም በላይ ትርፋማ ለመሆን መስራት ይጠበቅበታል – የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ

በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት 7.1 ቢሊየን ብር ትርፍ ማግኘት ችለናል – የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልተቋሙ ወጪዎችን በመቀነስና የገቢ አማራጮቹን በማስፋት ከዚህም በላይ ትርፋማ ለመሆን መስራት ይጠበቅበታል – የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከምስረታው ጀምሮ ከቆየበት ኪሳራ ወጥቶ ወደ ትርፋማነት መሸጋገሩን የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ አስታወቁ፡፡

ዋና ሥራ አስፈፃሚው የተቋሙን የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ሪፖርት ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሳይት ሲያቀርቡ እንደተናገሩት ተቋሙ በግማሽ ዓመቱ 7.1 ቢሊየን ብር ትርፍ አግኝቷል፡፡

ባለፉት ስድስት ወራት የውጭ ሀገራት የኃይል ሽያጭ በሁለት እጥፍ ዕድገት ሲያሳይ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የውጭ ምንዛሪ ግኝት ደግሞ በ138 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን ሥራ አስፈፃሚው ተናግረዋል፡፡

ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የ20 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር፣ ለኢንዱስትሪዎች የ2 ቢሊየን ብር፣ ለምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የ220 ሚሊየን ብር ለዳታ ማይኒንግ 180 ነጥብ 1 9 ሚሊየን ዶላር ሽያጭ መከናወኑን ዋና ስራ አስፈፃሚው በሪፖርታቸው አንስተዋል፡፡

ከውጭ ሀገራት የኃይል ሽያጭ እና ከዳታ ማይኒንግ የኃይል አቅርቦት ሽያጭ የተገኘውን የውጭ ምንዛሪ 247 ነጥብ 7 ሚሊየን ዶላር ጨምሮ የተቋሙ ጠቅላላ ገቢ 59 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር መድረሱን ዋና ሥራ አስፈፃሚው ገልፀዋል፡፡

ከኃይል ምርት አንፃር በተጠቀሰው ጊዜ 20 ነጥብ 3 ቴራ ዋት ሰዓት ኢነርጂ ለማምረት ዕቅድ ተይዞ 18 ነጥብ 3 ቴራ ዋት ኢነርጂ መመረቱን በመጥቀስ የዕቅዱ 90 ነጥብ 4 በመቶ መሳካቱን አስረድተዋል፡፡

እንደ ኢንጂነር አሸብር ገለፃ የተመረተው ኢነርጂ ከ2017 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ 35 በመቶ ጭማሪ ሲያሳይ ከዚህ ውስጥ የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የ51 በመቶ ድርሻ ነበረው፡፡

ዋና ሥራ አስፈፃሚው የተቋሙ የትኩረት መስኮች በሆኑት በኦፕሬሽን ልህቀት፣ የማይበገር እና አስተማማኝ መሰረተ ልማት ግንባታ፣ ፈጠራ እና ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና በሰው ሀብት ልማት ዙሪያ የተሰሩ ዝርዝር ሥራዎችን በሪፖርታቸው አቅርበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ግብረ መልስን ያቀረቡት ዶ/ር ጌትነት መላክ በበኩላቸው የተቋሙን ሪፖርት በኦፕሬሽን፤ በፋይናነስ አፈፃፀም፣ በኮርፖሬት እና ፕሮፌሽናል አስተዳደር እንዲሁም በውጭ ግንኙነት መስኮች የአፈፃፀም ግብረ መልስ ሰጥተዋል፡፡

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግብድ ተጠናቆ ሥራ መጀመር የኃይል ምርት በ36 በመቶ እንዲያድግ አስተዋጽዖ ማበርከቱን፣ ተቋሙ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የ12 በመቶ ትርፍ ማስመዘገቡን፣ የውጭ ሀገራት የኃይል ሽያጭ እያደገ መምጣቱን፣ 1635 ሜጋ ዋት ተጨማሪ ኃይል በበጀት ዓመቱ ወደ ኦፕሬሽን መግባቱን በአዎንታ አንስተዋል፡፡

የኢነርጂ ስብጥር ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ፣ ቴክኒካዊ የኃይል ብክነት ወደ 4 በመቶ መቀነስ ቢቻልም ከዚህም በላይ ብክነቱን መቀነስ መስራት እንደሚያስፈልግ፣ ወጪዎችን በመቀነስና የገቢ አማራጮቹን በማስፋት ከዚህም በላይ ትርፋማ ለመሆን መስራት እንደሚጠበቅበት፣ የሽያጭ ገቢ አሰባሰብ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ አንስተዋል፡፡

💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top