የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት በውጭ ምንዛሪ የ475 ሚሊየን ዶላር ሽያጭ ማከናወኑን የተቋሙ የኮርፖሬት ፋይናንስና ሀብት አስተዳደር ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አስታወቁ፡፡
ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚው አቶ ደመረ አሰፋ እንደገለፁት በውጭ ምንዛሪ የ455 ሚሊየን ዶላር ሽያጭ ለማከናወን ታቅዶ የ475 ነጥብ 7 ሚሊየን ዶላር ሽያጭ በማከናወን ከዕቅዱ የ5 በመቶ ብልጫ ያለው አፈፃፀም ተመዝግቧል፡፡
ለጎረቤት ሀገራት የ140 ነጥብ 19 ሚሊየን ዶላር ኃይል ሲቀርብ ለቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ደግሞ የ335 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ሽያጭ መከናወኑን ገልፀዋል፡፡
በውጭ ምንዛሪ የተከናወነው ሽያጭ ከአምናው ተመሳሳይ ሽያጭ የ41 በመቶ ብልጫ እንዳለው ጠቁመዋል፡፡
💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”