የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት እና በማስተላለፊያ መስመሩ ግንባታ ሥራ ላይ እያከናወነ ላለው ሥራ በመሻገር ቀን በዓል ላይ ዕውቅና ተሰጥቶታል።
ዕውቅናው ተቋሙ ፕሮጀክቱን ከነበረበት ችግር አላቆ ኃይል ለማምረት እንዲበቃና አሁን ለደረበት ደረጃ እንዲደርስ ለማድረግ ባከናወነው ሥራ ፕሮጀክቱን የማሻገር ማሳያ በማድረጉ የተበረከተ ነው።
የዕውቅና ዋንጫውን ከኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እጅ የተረከቡት የተቋሙ የኢንጂነሪንግ ዘርፍ ሥራ አስፈፃሚና የዋና ሥራ አስፈፃሚ ተወካይ አቶ ውድነህ የማነ ናቸው።
ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በተጨማሪ በግድቡ ግንባታ ዙሪያ የተለያየ አስተዋፅዖ ላበረከቱ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ በኢፌዴሪ ፌደሬሽን ም/ቤት በኩል፣ ለፀጥታ አካላት፣ ለፋይናንስ፣ ለሚዲያና ለሃይማኖት ተቋማት፣ ለዳያስፖራ አባላትና ለሌሎችም ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል።
“ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”






