ተቋሙ በሀገር አቀፍ የመሠረተ ልማትና ኮንስትራክሽን አውደርዕይ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል

ተቋሙ በሀገር አቀፍ የመሠረተ ልማትና ኮንስትራክሽን አውደርዕይ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በአዲስ ዓለም አቀፍ የኮንቬንሽን ማዕከል ዛሬ ሚያዝያ 9 ቀን 2018 ዓ.ም በተከፈተው ሀገር አቀፍ የኢትዮጵያ መሠረተ ልማትና ኮንስትራክሽን ሣምንት ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።

በኮንስትራክሽንና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር በተዘጋጀው በዚህ ዝግጅት ላይ በሀገራዊ የመሠረተ ልማት አመራር፣ ቅንጅት እና አፈጻጸም ዙሪያ እንዲሁም በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሂደት የታዩ ስኬቶች እና የተገኙ ተሞክሮዎች ቀርበው ውይይት የሚደረግባቸው ይሆናል፡፡

ከዛሬ ሚያዚያ 9-12 ቀን 2018 ዓ.ም በሚቆየው የኢትዮጵያ መሠረተ ልማትና ኮንስትራክሽን ሣምንት ላይ በኢነርጂ፣ በውሃ፣ በኢኖቬሽን፣ በኮንስትራክሽን፣ በሎጂስቲክስ፣ በዲጂታል መሠረተ ልማት እና ፖሊሲ ላይ ትኩረት አድርገው የሚሰሩ ተቋማት በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ይዘን እንመለሳለን።

Scroll to Top