
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅንና ለምርቃት መዘጋጀትን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙኃን በስካይ ላይት ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጠ ይገኛል።
መግለጫውን የተቋሙ የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን በመስጠት ላይ ናቸው።
ጋዜጣዊ መግለጫው በግድቡ ታሪካዊና ብሔራዊ ጠቀሜታ፣ የግድቡ የቴክኒክ እና የኦፕሬሽን ስኬት፣ ለሀገር ኢኮኖሚና ልማት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ እንዲሁም ተግዳሮቶች እና የወደፊት ዕቅዶች ዙሪያ ትኩረት ያደርጋል።
እኛም በጋዜጣዊ መግለጫው የሚነሱ ኃሳቦችን እየተከታተልን በሁሉም የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን የምናደርሳችሁ ይሆናል።
💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”