የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በተቋሙ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ዙሪያ ለመገናኛ ብዙኃን በስካይ ላይት ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጠ ይገኛል።
መግለጫውን የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ እየሰጡ ነው።
ጋዜጣዊ መግለጫው በ2017 በጀት ዓመት የኃይል ሽያጭና የገቢ አሰባሰብ፣ በኃይል ማመንጨት የኦፕሬሽን ሥራ አፈፃፀም፣ በማመንጫ፣ ማከፋፈያ ጣቢያዎችና ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክቶች አፈፃፀም እንዲሁም በ2018 ዋና ዋና ዕቅዶች ላይ ትኩረት ያደርጋል።
እኛም በጋዜጣዊ መግለጫው የሚነሱ ሀሳቦችን እየተከታተልን በሁሉም የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን የምናደርሳችሁ ይሆናል።
? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”