ባለፉት ስድስት ወራት ለ139 ጉዳዮች ምላሽ ተሰጥቷል

ባለፉት ስድስት ወራት ለ139 ጉዳዮች ምላሽ ተሰጥቷል

ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በ2018 በጀት ዓመት ስድስት ወራት ከውጭ ተገልጋዮች እና ከተቋሙ አመራርና ሠራተኞች ለቀረቡ 139 አስተዳደራዊ ጥያቄዎች ምላሽ መሰጠቱን የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

የጽ/ቤት ኃላፊው አቶ ሙላት ገዛኸኝ እንደገለፁት ባለፉት ስድስት ወራት ለ 152 አስተዳደራዊ ጉዳዮች ምላሽ ይሰጣል በሚል የታቀደ ቢሆንም ለቀረቡት 139 አስተዳደራዊ ጥያቄዎች ሙሉ በሙሉ ምላሽ ተሰጥቷል፡፡

ከዋና ስራ አስፈጻሚ በተሰጠ ውክልና መሠረት የተቋሙ ባለሙያዎች ለሚያከናውኗቸው ሙያዊ ተልዕኮዎች ድጋፍ ከመስጠት አንፃር ለ107 ሠራተኞችና የሥራ መሪዎች የፓስፖርት እድሳትና አዲስ ፓስፖርት እንዲያገኙ መደረጉን አስታውቀዋል፡፡

በተጨማሪም ከተቋሙ ጋር በሥራ ተቋራጭነት እና በተለያዩ ጉዳዮች አብረው ለሚሰሩ 71 የውጭ ሀገራት ዜጎች የሥራ እና የመኖሪያ ፈቃድ እንዲያገኙ መደረጉንም ተናግረዋል፡፡

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የምርቃት መርሐግብር በስኬት እንዲከናወን መደረጉን እና በተመሳሳይ የአይሻ 2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ምርቃት በስኬት ለማከናወን እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

እንደ አቶ ሙላት ገለፃ ከመንግስት የልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለቀረቡ የማህበረሰብ እና የፕሮጀክቶች ወቅታዊ የመረጃ ጥያቄዎች ከሚመለከታቸው የሥራ ዘርፎች ጋር በቅንጅት በመስራት ምላሽ ተሰጥቷል፡፡

በዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት የአስተዳደራዊ ጉዳዮች ሥራ አስኪያጅ ግርማ ግዛቸው (ዶ/ር) በበኩላቸው ባለፉት ስድስት ወራት ምላሽ ለሚያስፈልጋቸው አስተዳደራዊ ጉዳዮች ምላሽ መሰጠቱን መሆኑን ጠቁመዋል፡፡


የዋና ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት በስሩ ካሉ መምሪያዎች እና ቢሮዎች በጋራ በመሆን የስድስት ወራት አፈፃፀም በዛሬው ዕለት ገምግሟል፡፡

💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top