በጣቢያው ከካሳ ክፍያና ከውኃ አቅርቦት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ችግሮችን ለመፍታት ያለመ ውይይት እየተካሄደ ነው

በጣቢያው ከካሳ ክፍያና ከውኃ አቅርቦት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ችግሮችን ለመፍታት ያለመ ውይይት እየተካሄደ ነው

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የገናሌ ዳዋ የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ጋር ተያይዞ የሚነሱ የካሳ ክፍያ እና የውኃ አቅርቦት ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ያለመ ውይይት በነገሌ ቦረና ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

በተቋሙ የኃይል መሰረተ ልማት ደህንነት፣ ክትትልና ቁጥጥር እንዲሁም የአስተዳደራዊ ጉዳዮችና ዶክመንቴሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ ዋለ ታምሬ እንደገለጹት ፕሮጀክቶች በሚገነቡብት አካባቢ ለሚነሱ የማህበረሰብ ክፍሎች ደርጅቱ የካሳ ክፍያዎችን እንደሚፈጽም ተናግረዋል።

ሆኖም ከልማት ተነሺዎች የሚቀርብ የተጋነነ የካሳ ክፍያ ጥያቄ ለተቋሙ ፈተና እየሆነ መምጣቱን ያወሱት አቶ ዋለ ችግሩን ለመፍታትም ተቋሙ ከመስተዳድር አካላት ጋር በትብብር እየሰራ ነው ብለዋል።

አቶ ዋለ አክለውም በገናሌ ዳዋ የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ከካሳ ክፍያ እና ከውኃ አቅርቦት ጋር ያሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ተቋሙ ቁርጠኛ መሆኑን አንስተዋል።

በውይይቱ ላይ የተቋሙና የጣቢያው ኃላፊዎችን ጨምሮ የኦሮሚያ ውኃ ሥራዎች ድርጅት፣ የልማት ተነሽዎች ኤጀንሲ፣ የዞንና ወረዳ መስተዳድር አካላት እየተሳተፉ ይገኛል።

ከዚሁ በተጨማሪም በማመንጫ ጣቢያው አካባቢ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ በሚሆኑበት መንገድ ላይም ውይይት ይካሄዳል።

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top