በጣቢያው እየተከናወነ ያለው የጂ አይ ኤስ ተከላ 90 በመቶ ተጠናቋል

በጣቢያው እየተከናወነ ያለው የጂ አይ ኤስ ተከላ 90 በመቶ ተጠናቋል

በድሬዳዋ ቁጥር 2 የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ እየተከናወነ የሚገኘው የጂ አይ ኤስ (GIS) ተከላ ሥራ 90 በመቶ መጠናቀቁን የምስራቅ አንድ ሪጅን አስታወቀ።

የሪጅኑ ተወካይ ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ በየነ እንደገለጹት በአሁኑ ወቅት የተከላ ሥራው ተጠናቆ የኬብል አቅርቦት በመጠባበቅ ላይ ይገኛል።

አስፈላጊው የኬብል አቅርቦት እንደተሟላም በአጭር ጊዜ ውስጥ የዝርጋታ ሥራው ተጠናቆ የጂ አይ ኤስ ሥርዓቱ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር አስረድተዋል።

በጣቢያው የጂ አይ ኤስ (GIS) ቴክኖሎጂ ተከላ መከናወኑ ማከፋፈያ ጣቢያውን ከማዘመኑ ባለፈ፣ በአደጋ ጊዜ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በአፋጣኝ ለመከላከልና አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት ለመፍጠር እንደሚያስችል ተገልጿል።

በተጨማሪም ባለ 15 ኪሎ ቮልት አቅም ያላቸው አዳዲስ አምስት ወጪ መስመሮች መዘርጋታቸውን የገለጹት አቶ ቴዎድሮስ፤ እነዚህ መስመሮች ወደ አገልግሎት ሲገቡ የድሬዳዋንና የአካባቢውን የኃይል አቅርቦት እንደሚያሳድጉት አረጋግጠዋል።

Scroll to Top