በማከፋፈያ ጣቢያው ተጨማሪ የኃይል ትራንስፎርመር ለመትከል ቅድመ ዝግጅት ተጠናቋል

በማከፋፈያ ጣቢያው ተጨማሪ የኃይል ትራንስፎርመር ለመትከል ቅድመ ዝግጅት ተጠናቋል

ለድሬዳዋ ቁጥር 3 ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ አንድ ተጨማሪ የኃይል ትራንስፎርመር ለመትከል የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጠናቀቃቸውን የምስራቅ አንድ ሪጅን ገለፀ።

የሪጅኑ ተወካይ ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ በየነ እንዳስታወቁት በምስራቅ ኢትዮጵያ ያለውን ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎት ለማርካት ተጨማሪ የኃይል ትራንስፎርመር ለመትከል የሚያስችሉ ሥራዎች ተከናውነዋል።

125 ሜጋ ቮልት አምፔር አቅም ያለውን የኃይል ትራንስፎርመር የማጓጓዝ ሥራ በቅርቡ እንደሚጀመር የገለፁት አቶ ቴዎድሮስ የተከላ ሥራው በሪጅኑ ባለሙያዎች በራስ አቅም እንደሚከናወን ተናግረዋል።

በተጨማሪም ነባሩን ትራንስፎርመር ከአደጋ ለመከላከል የሚያስችል ሥራ መጠናቀቁንም ነው የገለፁት።

የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው ለድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ራሱን የቻለ ባለ 15 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር በመዘርጋት የመማር ማስተማሩን ሂደት እያገዘ መሆኑን አብራርተዋል።

ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች ላይ ከሚከናወኑ ሥራዎች ጎን ለጎን የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ታዎሮችን ከጎርፍ አደጋ ለመከላከል የጋቢዮን ንጣፍ በመሠራት ላይ መሆኑንም ነው ያስታወቁት።

ማከፋፈያ ጣቢያው ለድሬዳዋ እና አካባቢው በቀን በአማካይ 11 ሜጋ ዋት በማቅረብ ላይ ነው።

Scroll to Top