በጣቢያው ሲከናወን የቆየው የትራንስፎርመር ቅየራ ተጠናቋል

በጣቢያው ሲከናወን የቆየው የትራንስፎርመር ቅየራ ተጠናቋል

በወልቂጤ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ሲከናወን የቆየው የ63 ሜጋ ቮልት አምፔር የትራንስፎርመር ቅየራ ሥራ መጠናቀቁን የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ ገለፁ።

ሥራ አስኪያጁ አቶ ሙጀረብ የኑስ እንደገለፁት የትራንፎርመር ቅየራ ሥራው በመጠናቀቁ በፈረቃ ኃይል ሲያገኙ ለነበሩ አካባቢዎች ማምሻውን አስተማማኝ ኤሌክትሪክ ማቅረብ ይጀመራል።

በዚህም በ66 ኪሎ ቮልት የወሊሶ፣ ቱሉቦሎ፣ ጎሮ፣ አመያ እና አጨበር እንዲሁም ቁሳ ከተሞች ያለ ፈረቃ የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘት እንደሚጀምሩ ገልፀዋል።

በጉራጌ ዞን ሥር ለሚገኙ አካባቢዎች በ15 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመር  ኃይል እንደሚያገኙም ነው የተናገሩት።

በወልቂጤ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ አንድ ትራንስፎርመር ላይ ባጋጠመ የቴክኒክ ችግር ምክንያት አካባቢዎቹ ላለፉት 3 ሳምንታት የተወሰኑ አካባቢዎች ኃይል በፈረቃ ሲያገኙ መቆየታቸው ይታወሳል።

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top