በጣቢያው ሲከናወን የቆየዉ የመቆጣጠሪያዎች ቅየራ ተጠናቀቀ

በጣቢያው ሲከናወን የቆየዉ የመቆጣጠሪያዎች ቅየራ ተጠናቀቀ

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሰሜን ምስራቅ 2 ሪጂን ሥር በሚገኘው የሠመራ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ሲከናወን የቆየው የመቆጣጠሪያ ወይም ስዊችጊር ቅየራ መጠናቀቁን የመምሪያው ዳይሬክተር አስታውቁ፡፡

ዳይሬክተሩ አቶ ሐሰን ሙሓመድ እንደገለፁት በተቋሙ በራስ አቅም የማከፋፈያ ጣቢያውን የመቆጣጠሪያ ክፍል የማሻሻልና የማዘመን ሥራዎች በመስራት የኃይል አቅርቦቱን አስተማማኝነት ለመጨመር ተችሏል፡፡

በማከፋፈያ ጣቢያው ለረጅም ጊዜ ያገለገለውን በአየር የሚሰራ መቆጣጠሪያ በጋዝ ወደሚሰራ መቆጣጠሪያ መቀየር መቻሉ የጣቢያውን የኦፕሬሽን አቅም በማሳደግ አስተማማኝ እና የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችል ጠቅሰዋል።

የተቀየሩት መቆጣጠሪያዎች ቀደም ሲል የሚያጋጥመውን የኃይል መቆራረጥን ለማስወገድ እና የቁጥጥር ሥርዓቱን ለማዘመን እንደሚያስችል አስረድተዋል፡፡

በ2003 ዓ.ም ተገንብቶ ለአፋር ክልል በዋነኝነት ኃይል እያቀረበ የሚገኘው የሰመራ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ከኮምቦልቻ በ230 ኪሎ ቮልት የተቀበለውን ኃይል ወደ አፍዴራና ዲቾቶ ማከፋፈያ ጣቢያዎች በማስተላለፍ ከ80 በመቶ በላይ የሆነውን የአፋር ክልል ተደራሽ ያደርጋል፡፡

💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top