የጅማ- አባ ባለ 132 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ ምክንያት ከመጋቢት 22 ቀን 2018 ሌሊት 9፡15 ጀምሮ ኃይል ማስተላለፍ ማቋረጡን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የደቡብ ምዕራብ ሪጅን አስታወቀ፡፡
የሪጅኑ ዳይሬክተር አቶ ጌታሁን ሲሳይ እንዳስታወቁት የማስተላለፊያ መስመሩ ኃይል ማስተላለፍ ማቋረጡን ተከትሎ በዳውሮና በኮንታ ዞኖች ከትላንት ሌሊት ጀምሮ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ተቋርጧል፡፡
መስመሩ የተቋረጠበትን ምክንያት በመለየት ለችግሩ መፍትሔ ለመስጠት የሪጅኑ የጥገና ባለሙያዎች በመስመሩ ላይ የፍተሻ ሥራዎችን እያከናወኑ እንደሚገኙም ጠቅሰዋል፡፡
የማስተላለፊያ መስመሩ ዳግም ኃይል ማስተላለፍ እስኪጀምር ድረስ ኃይል በተቋረጠባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠብቁ አቶ ጌታሁን ጥሪ አቅርበዋል።
💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”
