በዘርፉ ያለውን የሴቶች ተሳትፎ ለማሳደግ ከታዳጊ ህፃናት ጀምሮ መስራት ይገባል፤ ወ/ሮ ሌንሴ ኢደኤ

በዘርፉ ያለውን የሴቶች ተሳትፎ ለማሳደግ ከታዳጊ ህፃናት ጀምሮ መስራት ይገባል፤ ወ/ሮ ሌንሴ ኢደኤ

በኤሌክትሪክ ኃይል ዘርፍ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ለማሳደግ መስራት እንደሚገባ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ገለጸፀ።

ከደጃዝማች ወንድይራድ ትምህርት ቤት የተወጣጡ ሴት ተማሪዎች በተቋሙ የመስክ ምልከታ አካሂደዋል፡፡

በጉብኙቱ ላይ የተገኙት የመምሪያው ዳይሬክተር ወ/ሮ ሌንሴ ኢደኤ የኃይል ዘርፉን ለማሳደግ ብቃት ያለው እና በሥርዓተ ፆታ የተመጣጠነ ባለሙያ ቢያስፈልግም አሁን ላይ በዘርፉ የተሰማሩ ሴቶች ቁጥር አነስተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ይህን ከግምት በማስገባት የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ ተቋሙ የተለያዩ ማበረታቻዎችን በመተግበር እየሰራ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

በኃይል ዘርፉ የሚታየውን የሥርዓተ-ፆታ አለመመጣጠን ለማስተካከል የሚመለከታቸው አካላት ከትምህርት ቤት ጀምረው ሊሰሩ እንደሚገባም ገልፀዋል፡፡

በመስክ ምልከታው የተሳተፉት ተማሪዎች በትምህርታቸው የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ መሆናቸውን የገለፁት ዳይሬክተሯ መርኃ ግብሩ ተማሪዎቹ በዘርፉ ያለውን የስራ እንቅስቃሴ እንዲያዩና ፍላጎት እንዲያድርባቸው ለማድረግ እንደሚረዳ አብራርተዋል፡፡

የተቋሙ ህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ሥራ አስኪያጅ አቶ ፍስሃ ጌታቸው ኤሌክትሪክ ወደ ሀገራችን እንዴት እንደገባ እና አሁን በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ለታዳጊ ህፃናቱ ገልፀው ተማሪዎቹ  የነገ ሀገር ተረካቢ መሆናቸውን ተገንዝበው በዘርፉ ላይ ብቁ ሙያተኛ ሆነው ለመገኘት ከአሁኑ በትምህርታቸው ጠንካራ በስነ-ምግባራቸው የታነፁ መሆን እንዳለባቸው ምክራቸውን ለግሰዋል። 

በተቋሙ የኃይል ማመንጫ ዘርፍ የዕቅድ ቢሮ ሥራ አሥኪያጅ ወ/ሮ ጥሩ ወርቅ ሽፈራው በበኩላቸው ተቋሙ በአሁኑ ወቅት ከውኃ፣ ከንፋስ እና ከተርማል በድምሩ 9750 ሜጋ ዋት  እያመነጨ ይገኛል ሲሉ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ሂደትን አስመልክቶ ገለፃ ሰጥተዋል።

የኢነርጂ ዘርፍ በውስጡ ብዙ እውቀት ያለበት በመሆኑን ጠቅሰው በሙያው መሳተፍ ለሚፈልጉ ተማሪዎች ከአሁኑ በርትተው ማጥናት እንደሚጠበቅባቸው አስረድተዋል፡፡

ኤሌክትሪክ እንዴት እንደሚጓጓዝና  እንደሚሰራጭ ግንዛቤ የሰጡት ጁኒየር መሀንዲስ ወ/ት ሀይመን ጠልሰም እንደተናገሩት ሙያው ከውጭ ሲታይ ከባድ ቢመስልም ሲገባበት ግን ደስ የሚል እና በፍላጎት የሚሰራ እንደሆነ አስገንዝበዋል፡፡

ተማሪዎቹም ኮተቤ የሚገኘውን ማከፋፈያ ጣቢያ የጎበኙ ሲሆን በተደረገላቸው ገለፃና በመስክ ጉበኝቱ መደሰታቸውን ገልፀው ስለ ኤሌትሪክ ያላቸውን ግንዛቤ በእጅጉ እንደለወጠው ተናግረዋል፡፡

💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top