በከባድ ንፋስ ምክንያት የኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች ወደቁ

በከባድ ንፋስ ምክንያት የኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች ወደቁ

ከለገጣፎ – ቃሊቲ በተዘረጋው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ አምስት የብረት ምሰሶዎች መውደቃቸውን የማዕከላዊ 1 ሪጅን አስታወቀ።

የሪጅኑ ዳይሬክተር አቶ ደረጄ ገዛኸኝ እንደተናገሩት ምንም እንኳ የብረት ምሰሶዎች በከባድ ንፋስ የወደቁ ቢሆንም በምሰሶዎቹ አካላት ላይ ስርቆት መፈፀሙ ለኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎቹ መውደቅ አሉታዊ አስተዋፅኦ አድርጓል።

በዚህ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ በተደጋጋሚ የስርቆት ወንጀል እንደሚፈፀም የገለፁት ዳይሬክተሩ ከለሚ ኩራ ክፍለ ከተማና ከወረዳው የአስተዳደር አካላት ጋር በመነጋገር ለችግሩ እልባት መስጠት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

የወደቁ የኃይል ምሰሶዎችን በአፋጣኝ በመጠገን መስመሩን ወደ አገልግሎት ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን አቶ ደረጀ ተናግረዋል።

አምስቱ የኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከሌሊት 7 ሰዓት አካባቢ መውደቃቸውንና በሰው እና በእንስሳት ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት አለመድረሱ ታውቋል።

Scroll to Top