በአዋሽ 7 ኪሎ አካባቢ የተፈፀመው ስርቆት ለምስራቅ ከተሞች ኃይል መቋረጥ ምክንያት ሆኗል

በአዋሽ 7 ኪሎ አካባቢ የተፈፀመው ስርቆት ለምስራቅ ከተሞች ኃይል መቋረጥ ምክንያት ሆኗል

በአፋር ክልል አዋሽ 7 ኪሎ ከተማ አቅራቢያ በ3 የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ  የብረት ምሰሶዎች ላይ ሥርቆት መፈፀሙን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማዕከላዊ 2 ሪጅን አስታወቀ።

የሪጅኑ ዳይሬክተር አቶ አለማየሁ ዘበርጋ እንደገለፁት ከለሊቱ 6:05 አካባቢ ከቆቃ ወደ ሁርሶ በተዘረጋው የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ በተፈፀመው ሥርቆት ድሬዳዋ፣ ሐረር እና ጅግጅጋን ጨምሮ በምስራቅ ኢትዮጵያ በሚገኙ ከተሞች ኃይል ተቋርጧል።

የምስራቅ ረጅን 1 ዳይሬክተር አቶ ወርዲ መሀመድ በበኩላቸው ኃይል ለተቋረጠባቸው አካባቢዎች በሌላ አማራጭ ኃይል እንዲያገኙ ለማድረግ እየተሰራ ነው።

በተቋሙ የትራንስሚሽን ቢዝነስ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አንዱዓለም ሲዓ ሥርቆቱ በከተማ አቅራቢያ መፈፀሙ የችግሩን አሳሳቢነት የሚያሳይ በመሆኑ የፀጥታና የመስተዳድር አካላት ድርጊቱን ለመከላከል ትኩረት እንዲሰጡት ጠይቀዋል።

ኃይል የተቋረጠባቸው አካባቢዎች በተቻለ ፍጥነት በሌላ አማራጭ ኃይል እንዲያገኙ እየተደረገ ቢሆንም በጊዜያዊነት በቂ ኃይል ላይኖር ስለሚችል ከፍተኛ ኃይል ተጠቃሚዎች አጠቃቀማቸውን እንዲያስተካክሉ አሳስበዋል።

💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top