በአሶሳና አካባቢው የተቋረጠውን ኃይል መልሶ የማገናኘት ሥራ ተሰርቷል

በአሶሳና አካባቢው የተቋረጠውን ኃይል መልሶ የማገናኘት ሥራ ተሰርቷል

የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶ በመውደቁ ምክንያት በአሶሳና በዙሪያው በሚገኙ ወረዳዎች ለቀናት ተቋርጦ የቆየው ኃይል መልሶ መገናኘቱን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ አስታወቀ።

በዘርፉ የሪጅኖች ማስተባበሪያ መምሪያ ዳይሬክተር አቶ እስማኤል ሙዘይን እንደገለፁት ዛሬ ከቀኑ 8፡50 ጀምሮ አካባቢው ዳግም ኃይል እንዲያገኝ ተደርጓል፡፡

አካባቢው ኃይል እንዲያገኝ የተደረገው በባለሙያዎች የቀረበውን ቴክኒካዊ የአማራጭ መፍትሔ በመተግበር መሆኑን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።

💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top