ሴትነት እና የአየር ሁኔታ አስቸጋሪነት ሳይበግረን የተሰጠንን ተቋማዊ ኃላፊነት እየተወጣን ነው ሲሉ በሰሜን ምስራቅ ሪጅን 2 የሰመራ ማከፋፈያ ጣቢያ የኦፕሬሽን ሠራተኛ ወ/ሮ ነጃት እሸቱ ተናገሩ፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሠራተኞች በማንኛውም የአየር ሁኔታ እና መልክዐ ምድር የሚሰሩ በመሆናቸው ሰመራ ማከፋፈያ ጣቢያ ስመደብ በሙሉ ፍላጎት እና በልበ ሙሉነት ሥራዬን እንደምወጣ ቁርጠኛ ነበርኩ ብለዋል፡፡
አሁን በሚሰሩበት ማከፋፈያ ጣቢያ ሌሎች ሁለት እህቶቼ አብረውኝ ስለሚሰሩ ሴትነት ሳይበግረን በከፍተኛ የሥራ ሞራል እና መተሳሰብ ሥራቸውን እየፈፀሙ ስለመሆኑ ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሰሜን ምስራቅ 2 ሪጅን አስር የአካባቢዉን ተወላጆች አወዳድሮ በማሰልጠን በኦፕሬተርነት እንዲያገለግሉ መድቧል፡፡
? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”



