ሪጅኑ በክልሉ መቋቋሙ የክልሉን የኃይል ጥያቄ ለመመለስ አስችሏል

ሪጅኑ በክልሉ መቋቋሙ የክልሉን የኃይል ጥያቄ ለመመለስ አስችሏል

ለአፋር ክልል በቅርበት አገልግሎት እንዲሰጥ የተቋቋመዉ የሰሜን ምስራቅ 2 ሪጅን የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን መምሪያ የክልሉን የኃይል ጥያቄን ለመመለስ ማስቻሉን የሪጅኑ ዳይሬክተር አስታወቁ፡፡

ዳይሬክተሩ አቶ ሀሰን መሀመድ እንዳስታወቁት በክልሉ የሚገኙት የሰመራ፣ አፍዴራ እና ዲቼቶ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች ቀደም ሲል ተጠሪነታቸዉ በደሴ ለሚገኘው የሰሜን ምስራቅ 1 ሪጅን ነበር፡፡

ይህም የኤሌክትሪክ መቋረጥ ሲያጋጥም በአፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት አዳጋች እንደነበር አስታዉሰዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሰሜን ምስራቅ 2 ሪጅን በሰመራ እንዲቋቋም መደረጉ የኤሌክትሪክ ብልሽት ሲያጋጥም አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት፣ የኃይል መቆራራጥን ለመቀነስ፣ በክልሉ የሚገኙ የተለያዩ አምራች እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሥራዎቻቸዉን እንዲያከናዉኑ ለማድረግ መደላደልን ፈጥሯል ብለዋል፡፡ 

ከተቋቋመ አንድ ዓመት ከስምንት ወራትን ያስቆጠረዉ ሪጅኑ የክልሉን ሰማንያ በመቶ አካባቢዎችን ተደራሽ በማድረግ የተሻለ የኃይል አቅርቦቱ እንዲኖር ማድረጉን አመልክተዋል፡፡

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top