በኃይል መሠረተ ልማት ላይ ስርቆት የፈጸሙ ተጠርጣሪዎች በሕግ በቁጥጥር ስር ዋሉ

በኃይል መሠረተ ልማት ላይ ስርቆት የፈጸሙ ተጠርጣሪዎች በሕግ በቁጥጥር ስር ዋሉ

በጎፋ ዞን ደምባ ጎፋ ወረዳ በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ ስርቆት የፈጸሙ ተጠርጣሪዎች በሕግ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የወረዳው ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ገለጸ።

የጽ/ቤቱ አዛዥ ተወካይ ዋ/ሣጅን ያዕቆቦ ካሳሁን እንደገለጹት ተጠርጣሪዎቹ ጨለማን ተገን በማድረግ የኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶ ብረቶችን በቡድን በመስረቅ ወንጀል  ተጠርጥረው በኦፕሬሽን ሥራ በሕግ  ቁጥጥር ስር ውለዋል።

ዋ/ሣጅን ያዕቆቦ ካሳሁን,
በጎፋ ዞን ደምባ ጎፋ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት አዛዥ ተወካይ

ተጠርጣሪዎቹ የሎጤ ጋይላ ጫልቤ ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ በወረዳው ቶዣ ስቤ፣ ሎጤ ማዘጋጃ ዛንጋ ዘልጎ፣ ዛንጋ ዶርማሌ፣ ዛንጋ አዋንዴ ካርዛ፣ ቦላ፣ ዶምቤ ዙልዝ ፂላ እና ቦርዳ ቀበሌያት በእርሻ ማሳ ዉስጥ የሚገኙ የኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶ ብረቶችን ላይ በተለያዩ ጊዜያት ስርቆት ሲፈፅሙ መቆየታቸውን አብራርተዋል።

ፖሊስም ከአካባቢው ሕብረተሰብ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ግለሰቦችን ከተሰረቁ ብረቶች ጋር በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን ጠቁመዋል።

በተጠርጣሪዎች ላይ የሚካሄደውን የምርመራ ሥራ በፍጥነት በማጠናቀቅ ክስ እንደሚመሰረትም ገልጸዋል።

በኃይል መሠረተ ልማት አውታሮች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን መከላከል የሁሉም ኃላፊነት መሆኑን የተናገሩት ዋ/ሣጅን ያዕቆቦ ሕብረተሰቡም የስርቆት ወንጀሉን የመከላከልና ወንጀለኞቹን ለሕግ አሳልፎ የመስጠት ትብብሩን አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል። 

💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top