በመቀሌ ማከፋፈያ ጣቢያ ባለ 33 ኪሎ ቮልት ፓወር ትራንስፎርመር ላይ ባጋጠመ ችግር የተነሳ ኃይል መቋረጡን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ አስታወቀ።
በዘርፋ የሰሜን ሪጀን የኦፕሬሽንና ጥገና መምርያ ዳይሬክተር አቶ ሮቤል ገ/እግዚአብሔር እንደገለፁት በትራንስፎርመሩ ላይ በገጠመው ችግር የተነሳ በመቀሌ ኢንዲስትሪ ፓርክ እና 70 ካሬ አካባቢ ኃይል ተቋርጧል።
በተጨማሪም በሀገረ ሠላም እና በህንጣሎ ዋጀራት ወረዳዎችና በዙሪያቸው ባሉ ቀበሌዎች እንዲሁም በኢታካ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ኃይል መቋረጡን ኃላፊው ገልፀዋል።
ይሁንና ከማከፋፈያ ጣቢያው በ15 ኪሎ ቮልት ኃይል ሲያገኙ የነበሩ አካባቢዎች ኃይል እንዳልተቋረጠባቸው አስረድተዋል።
ትራንስፎርመሩ ላይ የገጠመውን ችግር ለማወቅ የሚያስችሉ ሥራዎች መጀመራቸውን ተናግረዋል።
ችግሩ የትራንስፎርመር ዋይንዲንግ ላይ የተከሰተ ከሆነ ሌላ ትራንስፎርመር መቀየር ሊያስፈልግ እንደሚችል ጠቁመዋል።
? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”