በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ1ሺ 1 መቶ በላይ የሥራ መደቦች በዕድገት፣ በዝውውርና በምደባ እንዲሟሉ ተደርጓል

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ1ሺ 1 መቶ በላይ የሥራ መደቦች በዕድገት፣ በዝውውርና በምደባ እንዲሟሉ ተደርጓል

በ2016 በጀት ዓመት በዕድገት፣ በዝውውርና በምደባ 1 ሺህ 132 የስራ መደቦች መሟላታቸውን በሰው ሀብት ዘርፍ የሰው ሀብት አስተዳደር መምሪያ አስታወቀ፡፡

የመምሪያው ዳይሬክተር አቶ ተማም አፍደል እንደተናገሩት በበጀት ዓመቱ 677 የሥራ መዶቦችን በዕድገት፣ 362 በዝውውር እና 93 በምደባ እንዲሟሉ ተደርጓል፡፡

በበጀት ዓመቱ የሥራ መደቦችን በተፈላጊ የሰው ኃይል ለማሟላት በተሰራው ሥራ 253 ሠራተኞች በውጭ በቅጥር እንዲሟላ መደረጉን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

የፅዳት፣ የጥበቃና የአትክልተኛ ሥራዎችን በሦስተኛ ወገን ለማሰራት በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት 1 ሺህ 962 የሥራ መደቦች እንዲሸፈኑ መደረጉንም አቶ ተማም ተናግረዋል፡፡

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የሥራ መሪዎች ምደባ መመሪያ እና የብቃት መመዘኛ ፈተና አፈጻፀም ማንዋል ፀድቀው ወደ ስራ መግባታቸውንም ገልፀዋል፡፡

ከተያዘው ዕቅድ አንፃር በበጀት ዓመቱ በዕድገት፣ በዝውውርና በምደባ የተሟላው የሰው ኃይል 135 በመቶ እና በቅጥር 97 ነጥብ 3 በመቶ መከናወኑን አስረድተዋል፡፡

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top