በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የሀገሪቱን የኃይል ትስስር መቶ በመቶ ለማድረስ ይሰራል

በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የሀገሪቱን የኃይል ትስስር መቶ በመቶ ለማድረስ ይሰራል

በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት በመላው ኢትዮጵያ ያለው የኃይል ትስስር መቶ በመቶ እንዲረጋገጥ ይሰራል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዲጂታል 2030 መጀመር ይፋ በሆነበት መድረክ ላይ እንደገለፁት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተደራሽነት ሳይሟላ የሚረጋገጥ እድገት አይኖርም፡፡

በአንድም በሌላም አማራጭ በመላው ሀገሪቱ የኃይል ትሥሥር መፍጠር ወሳኝ በመሆኑ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ከዋናው ግሪድ በተጓዳኝ የሚኒ ግሪድ እና ኦፍ ግሪድ የኃይል ትስስር አማራጮች ተግባራዊ እንደሚደረጉም ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ምግብ በመሆኑ፣ ያለ ኃይል ትሥሥር እውን የሚሆን የዲጂታል ንቅናቄ እንደማይኖር እሙን ነው፡፡

የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ትልም እውን እንዲሆን እና ዕድገት እንዲረጋገጥ ኤሌክትሪክ ማዳረስ ወሳኝ መሆኑንም ነው ያብራሩት፡፡

💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top