በሳፕ ምዕራፍ 2 ትግበራ ላይ የልምድ ልውውጥ ተካሄደ

በሳፕ ምዕራፍ 2 ትግበራ ላይ የልምድ ልውውጥ ተካሄደ

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሰራርን ለማዘመን እየተተገበረ ባለው የሳፕ ሲስተም የምዕራፍ 2 ትግበራ ላይ በኃይል ማመንጫዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ የፕላንት ሜንቴናንስ ሞጁል የተጠቃሚዎች ስልጠና የልምድ ልውውጥ አካሄዱ፡፡

በልምድ ልውውጥ መድረኩ ላይ በትግበራ ሂደት የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ላይ ውይይቶች ተካሂዷል፡፡

የውይይት መድረኩ ያስጀመሩት በሰው ሀብት ዘርፍ የሰው ኃይል ሥልጠናና ልማት ማዕከል ሥራ አስኪያጅ አቶ ደምስ ሰይፉ እንደተናገሩት በተቋሙ 19 ሞጁሎችን በምዕራፍ 2 ለመተግበር ዕቅድ ተይዟል፡፡

ከዕቅዱ 95 በመቶ የሚሆነው በኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች የጥገና ሂደት ላይ ያተኮረ ነው ብለዋል፡፡

በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት 377 ወንድና 68 ሴቶች በድምሩ ለ 445 ሠራተኞች በሞጁሎቹ ላይ የተጠቃሚዎች ሥልጠና መሰጠቱን ገልፀዋል፡፡

በኃይል ማመንጫዎች ዘርፍ የቴክኒካል ድጋፍ ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዱ ይማም በበኩላቸው የፕላንት ሜንቴናንስ ሞጁል ትግበራን በኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች መስጠት መቻሉ እያንዳንዱ ሰልጣኝ ግንዛቤውንና ክህሎቱን እንዲያዳብር አድርጎታል፡፡

የመተግበሪያ መበልፀግ እና የዲጂታል መማማሪያ እንዲኖር የማድረግ ሥራዎችን በየጣቢያዎች በመስራት ትግበራውን ማዳበር መቻሉንም ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ተግባራዊ ከተደረጉት ኢኒሼቲቮች ውስጥ የፈተና ምዘናና ውጤት አሰጣጥ፣ የአንድሮይድ መተግበሪያ ማበልፀግ እና የዕውቀት አስተዳደር ሥርዓትን በማሻሻል ሳፕ እየተተገበረ እንደሚገኝ አቶ አብዱ አስረድተዋል፡፡

በልምድ ልውውጥ መድረኩ ላይ ከተቋሙ የተለያዩ ክፍሎች የተውጣጡ 35 የሳፕ አስተግባሪዎች ተሳትፈዋል፡፡

💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top