በሪጅኑ የሳፕ ፕላንት ሜንቴናንስ ሞጁል የተጠቃሚዎች ስልጠና እየተሰጠ ነው

በሪጅኑ የሳፕ ፕላንት ሜንቴናንስ ሞጁል የተጠቃሚዎች ስልጠና እየተሰጠ ነው

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሰሜን ሪጅን ለሚገኙ የማከፋፈያ ጣቢያ እና ማስተላለፊያ መስመሮች የጥገና ባለሞያዎች እና ኃላፊዎች የሳፕ ፕላንት ሜንቴናንስ ሞጁል የተጠቃሚዎች ስልጠና መሰጠት ተጀምሯል።

በማከፋፈያ ጣቢያዎችና ማስተላለፊያ መስመሮች ኦፕሬሽን ቢሮ የሳፕ ትግበራ ኮሚቴ አባልና አሰልጣኝ የሆኑት አቶ ወልዳይ ገ/ትንሳኤ እንደገለጹት ሥልጠናው በሪጅኑ የማከፋፈያ ጣቢያዎች እና ማስተላለፊያ መስመሮች የሚደረገውን የጥገና ሂደት ሙሉ ለሙሉ በማዘመንና በማቀላጠፍ በኩል ጉልህ ሚና ይጫወታል።

ሥልጠናው የማከፋፈያ ጣቢያዎች እና ማስተላለፊያ መስመሮችን ንብረት አያያዝና አጠቃቀም ለመከታተልና አስተማማኝነታቸውን ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ገልጸዋል።

በሪጅኑ መደበኛ የፍተሻ እና የጥገና ሥራዎችን እንዲሁም ክትትልና የቁጥጥር ሥርዓቱን በማጠናከር እና በማቀላጠፍ  የኃይል መቆራረጥን ለመቀነስ እንደሚረዳ ተናግረዋል።

እንደ አቶ ወልዳይ ገለጻ የሞጁሉ መተግበር የጥገና መረጃዎችን በመሰብሰብና በመተንተን የተሻለ ውሳኔ አሰጣጥ እና ትንበያ እንዲኖር ያስችላል።

ሥልጠናው በጥገና አሰራር ሥርዓት፣ በመለዋወጫ ዕቃዎች አቅርቦት፣ አስተዳደር እና ተያያዥ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ ለሦስት ሳምንታት የሚሰጥ ይሆናል።

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top