በሪጅኑ በተለያዩ ምክንያቶች ወድቀው የነበሩ 20 የከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ ምሰሶዎች ተጠግነው ወደ ሥራ ገብተዋል

በሪጅኑ በተለያዩ ምክንያቶች ወድቀው የነበሩ 20 የከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ ምሰሶዎች ተጠግነው ወደ ሥራ ገብተዋል

በተለያዩ ጊዚያት ወድቀው የነበሩ 20 የከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ ምሰሶዎችን መልሶ በመጠገን ወደ ሥራ ማስገባቱን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የምዕራብ ሪጅን አስታወቀ።

የሪጅኑ ዳይሬክተር አቶ ኃይሉ በቀለ እንዳስታወቁት በሪጅኑ በሚገኙ ከፍተኛ የኃይል ተሸካሚ ምሰሶዎች ላይ በደረሰው ጉዳት የተቋረጠውን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ችግር ለመፍታት የእንጨት ምሰሶዎችን በመትከል ኃይል ሲቀርብ ቆይቷል፡፡

 አሁን ላይ በተለያዩ የማስተላለፊያ መስመሮች ላይ ወድቀው የነበሩ የከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ ምሰሶዎችን በመጠገን ወደ ነበሩበት መመለስ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

በመንዲ-ጊዳሚ 132 ኪሎ ቮልት ማስላለፊያ መስመር ላይ አምስት ታዎሮች፣ በመንዲ-አሶሳ 132 ኪሎ ቮልት ማስተላለፊያ መስመር ላይ 13 ታዎሮች እና በነቀምት – ጊዳ አያና 132 ኪሎ ቮልት ማስተላለፊያ መስመር ላይ  ሁለት ታወሮች በድምሩ በ20 ታዎሮች ላይ የጥገና ሥራ የተከናወነ መሆኑን ዳይሬክተሩ አስረድተዋል፡፡

የጥገና ሥራው የኃይል መቆራረጥን በመቀነስ ለደንበኞች አስተማማኝ ኃይል ለማቅረብ ማስቻሉን እና ከዚህ በፊት ለተደጋጋሚ የእንጨት ምሰሶ ጥገና እና ቅያሪ ይወጣ የነበረውን ከፍተኛ ወጪ ማዳኑን ገልጸዋል፡፡

በእንጨት ምሰሶ የነበረውን መስመር ወደ ታወር ብረት የመቀየር ሥራ እጅግ ፈታኝ ቢሆንም የሪጅኑ ሠራተኞች የጥገና አቅም በማደጉ ሥራውን በስኬት ማከናወን ተችሏል ብለዋል፡፡

በጥገና ሂደቱ ወቅት አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ተቋቁመው ሥራውን ላከናወኑ የሪጅኑ የጥገና ባለሙያዎች እና አሽከርካሪዎች ምስጋናቸውን ያቀረቡት አቶ ኃይሉ በቀጣይ በሪጅኑ ያሉ ደንበኞችን ፍላጎት ለማሟላት በትኩረት እንደሚሰራም አረጋግጠዋል፡፡

Scroll to Top