በሪጅኑ ሲከናወን የቆየው የኮንዳክተር ቅየራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል

በሪጅኑ ሲከናወን የቆየው የኮንዳክተር ቅየራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሰሜን ምስራቅ 2 ሪጅን ሲከናወን የቆየው የኮንዳክተር ቅየራና መልሶ ግንባታ ሥራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የሪጅኑ ዳይሬክተር ገለጹ፡፡

ዳይሬክተሩ አቶ ሐሰን መሐመድ እንደገለጹት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግር በሪጅኑ በሚገኙ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ ጉዳት ደርሶባቸው ነበር፡፡

ጉዳት የደረሰባቸውን መስመሮች በጊዜያዊነት ጥገና በማድረግ ለአካባቢው የኤሌክትሪክ ኃይል ሲቀርብ የነበረ ቢሆንም አስተማማኝ ኃይል ለማቅረብ በሚሰራው ሥራ ላይ እንቅፋት መፍጠሩንም አስታውሰዋል፡፡

ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ መስመሩን በአዲስ ኮንዳክተር የመተካትና የመጠገን ሥራ ለአንድ ወር ያህል ሲከናወን መቆየቱን አንስተዋል፡፡

የኮንዳክተር ቅየራው 86 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን መሆኑን የገለጹት ዳይሬክተሩ ሥራውን ከሰሜን ምስራቅ 1 ሪጅን ጋር በመተባበር ሠርቶ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ማብቃት መቻሉን አስታወቀዋል፡፡

የጥገና ሥራው በተቋሙ ባለሙያዎች በመሰራቱ ከ11 ሚሊየን ብር በላይ ማዳን መቻሉን ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top