በመድን ፖሊሲዎች አተገባበር ዙሪያ የግንዛቤ ማሳደጊያ ስልጠና ተሰጠ

በመድን ፖሊሲዎች አተገባበር ዙሪያ የግንዛቤ ማሳደጊያ ስልጠና ተሰጠ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከኢትዮጵያ መድን ድርጅት ጋር በመተባበር በመድን ፖሊሲዎች  አተገባበር ዙሪያ ለአምስት ተከታታይ ቀናት  ሥልጠና  ተሰጥቷል፡፡ 
     
በሥልጠናው  ማጠቃላያ ላይ በንብረት አስተዳደርና ጥገና መምሪያ የንብረት ሪስክና ኢንሹራንስ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሳህሌ ደግፍ እንደተናገሩት ሥልጠናው በኢንሹራንስ ፖሊሲዎች አተገባበር ዙሪያ ቴክኒካዊና ህጋዊ አካሄዶችን ለይቶ ለማወቅ የሚያስችል ነው፡፡

ሥልጠናው በሞተር፣ በማሽነሪ ጉዳት፣ በእሳትና መብረቅ፣ በሠራተኞች የ24 ሰዓት የኢንሹራንስ ሽፋን፣ በገንዘብ እና ገንዘብ ነክ ስራ ላይ ለተሰማሩ ሠራተኞች የእምነት ማጉደል የኢንሹራንስ ፖሊሲዎች እና አተገባበር ትኩረት ያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሠልጣኞች ከሥልጠናው ባገኙትን እውቀት በኢንሹራንስ መሸፈን ያለባቸውን እና የሌለባቸውን ንብረቶች በመለየት ተቋሙ ተጠቃሚ የሚሆንበት የውሳኔ ሀሳብ ለማቅረብ ያስችላቸዋል ብለዋል፡፡

የኢንሹራንስ ሽፋን በተሰጣቸው ንብረቶች ላይ ጉዳት ሲደርስ በፖሊሲው መሰረት ለካሳ ክፍያ የሚያስፈለጉ መረጃዎችን በፍጥነት አጠናክረው በማዘጋጀት ለሚመለከተው አካል ማቅረብ እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡

በሁለት ዙር ለ10 ቀናት በተሰጠው ሥልጠና ላይ ከተቋሙ የተለያዩ የሥራ ክፍሎች የተወጣጡ ከ50 በላይ ባለሙያዎች እና የሥራ መሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ስልጠናው ከኢትዮያ መድን ድርጅት በመጡ ባለሙያዎች መሰጠቱ ተገልጿል፡፡

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top