የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አመራርና ሠራተኞች የሀሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልጽግና በሚል መሪ ሀሳብ በሀገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በተቋሙ ዋና መስሪያ ወይይት አካሂደዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የተቋሙ ሠራተኞች የኑሮ ውድነትን፣ ተንቀሳቅሶ ለመስራት ያለውን የጸጥታ ችግር እና የሠራተኛውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት እየተሰሩ ካሉ ሥራዎች ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን አንስተዋል፡፡
ከኑሮ ውድነት ጋር ተያይዞ ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት የተቋሙ የፋይናንስ ዘርፍ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ደመረ አሰፋ እንደተናገሩት የኑሮ ውድነቱ ከዓለም አቀፋዊ የዋጋ ግሽበት ጋር የሚያያዝ በመሆኑ መንግስት ችግሩን ለመቅረፍ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያ ጨምሮ በልማት ትሩፋት ሥራዎች ገበያውን የማረጋገት ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡
ከጸጥታ ጋር ተያይዞ ለተነሱት ጥያቄዎች ዋና ሥራ አስፈጻሚው ኢንጂነር አሸበር ባልቻ በሰጡት ምላሽ አብዛኛዎቹ የፀጥታ መደፍረስ ችግሮች ከነጠላ ትርክቶች የሚነሱ በመሆኑ ለሀሳብ ልዕልና ቦታ አልተሰጠውም ነበር፡፡
በመሆኑም መንግስት የዜጎችን ሠላምና ደህንነት ለማረጋገጥ ሀገረዊ ምክከር ኮሚሽን ከማቋቋም አንስቶ በጠመንጃ ሳይሆን በሀሳብ ልዕልና ላይ የተመሰረተ ሀገረ መንግስት ለመገንባት የተያዩ ጥረቶችን እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡
ለተፈጠሩት የጸጥታ ቸግሮች መፍትሄ ለማስገኘት የሚደረገው ጥረት የሁሉንም ተሳትፎ የሚፈልግ በመሆኑ ሁሉም ከመንግስት ጎን እንዲቆም ጠይቀዋል፡፡
የመኖሪያ ቤት ችግርን በተመለከተ ዋና ሥራ አስፈፃሚው በሰጡት ምላሽ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመነጋገር የተጀመሩ ሥራዎች እንዳሉ በመጠቆም ጥያቄው መፍትሔ እስኪያገኝ ድረስ ከሚመለከተው አካላት ጋር በቅርበት መስራቱን እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”





