የመንግስትን ፖሊስ የሚያስፈጽሙ ሠራተኞች በመላው ሀገሪቱ በሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ላይ ግልፅ ግንዛቤ በመጨበጥ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አሳሰቡ፡፡
ዋና ሥራ አስፈጻሚው ኢንጂነር አሸብር ባልቻ የተቋሙ አመራሮችና ሠራተኞች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ባካሄዱት ውይይት ማጠቃለያ ላይ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ዓመታት በኮቪድ፣ በዓለም የኢኮኖሚ ቀውስ፣ በእርስ በእርስ ግጭት እና በመሳሰሉት ችግሮች ውስጥ ሆና ዕድገት አስመዝግባለች፡፡
የተመበዘገበው ዕድገት ትሩፋቶቸና የመጣው ለውጥ ሀገራችን የገጠማትን ተግዳሮቶች አልፋ መሄድ እንደምትችል ከማሳየት ባለፈ ለውጡ በተቋሙ በግልጽ የሚታይ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡
የተቋሙ ሠራተኞች ከጨለምተኛ አመለካከት ወጥተው ትክክለኛ መረጃ በመያዝ ለአላስፈላጊ ነጣለ ትርክት ተጋላጭ እንዳይሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከለውጡ በፊት ምን ደረጃ ላይ እንደነበር የሚዘጋ አይደለም ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው ከለውጡ በኋላ በምን ያህል መስዋትነት እና ቁርጠኛ አመራር አሁን ላለበት ደረጃ መብቃቱ ተጨባጭ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
ይሁንና ተቋሙ በፕሮጀክቶች አፈጻጸም እና መዘግየት የሚያጋጥሙትን ከፍተቶች ለማስወገድ የሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች በትኩረት እንዲሰሩ አቅጣጫ መቀመጡን ገልፀዋል፡፡
ስለሆነም ሠራተኞች የሚመለከቷቸውን የብልሹ አሰራር ክፍተቶች የሚያሳዩ ማስረጃዎችን በመያዝ ድርጊቱን እንዲዋጉ ኢንጂነር አሸብር ጠይቀዋል፡፡
በውይይቱ ከሠራተኞች የተነሱትን የተለያዩ ጥያቄዎች ዋና ሥራ አስፈጻሚው እና ሌሎች የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ምላሽ ሰጥተውባቸዋል ፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አመራሮችና ሠራተኞች ካካሄዱት ውይይት ጎን ለጎን የደም ልገሳ አካሂደዋል፡፡
የደም ልገሳ መርሃግብሩ በተለያዩ ምክንያቶች ደም ለሚያስፈልጋቸው የህብረተሰብ ክፍሎች እንዲውል ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡
መርሃ ግብሩን አስመልክቶ ንግር ያደረጉት በደምና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት የትምህርት እና የቅስቀሳ ባለሙያ ሲስተር አሰጋሽ ጎሳ እንደተናገሩት ደም በፋብሪካ የማይመረት በመሆኑ በደም አጦት ማንም ሰው ህይወቱን ሊያጣ አይገባም፡፡
ሠራተኛው የወገን ደራሽነቱን ደም በመለገስ በተግባር ማሳየት እንደሚገባው የተናገሩት ባለሙያዋ ደም በለገስ ከኮሌትሮል፣ ከደም ውስጥ የብረት መጠን ክምችት፣ ከካንሰርና ከሌሎች በሽታዎች የመታደግ የጤና ጠቀሜታዎች እንዳሉት አስረድተዋል፡፡
ደም የሚሞት እና የሚያረጅ እንዲሁም የሚተካ በመሆኑ በሚተካ ደም የማይተካ የሰው ህይወት ልናድንበት ይገባል ብለዋል፡፡
? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”



