ስለ ጣቢያው አሠራርና ቴክኖሎጂ ማወቅ ለጣቢያው ተገቢውን እገዛ ለማድረግ ያስችላል

ስለ ጣቢያው አሠራርና ቴክኖሎጂ ማወቅ ለጣቢያው ተገቢውን እገዛ ለማድረግ ያስችላል

በወላይታ ሶዶ ባለ 500 ኪሎ ቮልት ኮንቨርተር ጣቢያ ላይ የሚደረጉ ጉብኝቶች የጣቢያውን ሠራተኞችን የሥራ ተነሳሽነት እንደሚያሳድጉት የጣቢያው ኃላፊና ሠራተኞች ተናገሩ።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፊያ መስመርና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ የሥራ ኃላፊዎች ጣቢያውን ጎብኝተዋል፡፡

የኮንቨርተር ጣቢያው ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ግርማ እንደተናገሩት ጉብኝቱ በስራ ሂደት ላይ ከኦፕሬሽን እና ከአስተዳደር ጋር በተያያዘ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለሚመለከተው አካል በቀላሉ ለማሳወቅ እና ችግሮች የሚፈቱበትን መንገድ ለማመቻቸት ዕድል ይፈጥራል።

ጉብኝቱ ጣቢያው ስለሚጠቀመው እና ልዩ ስለሚያደርገው ቴክኖሎጂ ለማስተዋወቅ ዕድል ከመፍጠር ባለፈ የተቋሙ ሠራተኞች ስለ ቴክኖሎጂው ያላቸው ግንዛቤ በማሳደግ የሠራተኛውን የሥራ ተነሳሽነት እንደሚጨምር አመልክተዋል።

በጣቢያው የኦፕሬሽንና የጥገና ባለሙያ አቶ ዓለሙ አድማስ በበኩላቸው ጉብኝቱ የተቋሙ ማህበረሰብ ለጣቢያው የሰጡትን ትኩረት ለማወቅ ያግዛል።

የጥገናና የኦፕሬሽን ሥራውን ለማስቀጠልና የዕውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲኖር ለማድረግ የተቋሙ ማህበረሰብ ስለ ጣቢያው አሠራርና ስለሚጠቀመው ቴክኖሎጂ ማወቅ እንደሚጠበቅበት ባለሙያው አመልክተዋል።

በጉብኝቱ ላይ ከተሳተፉት መካከል የሰሜን ሪጂን የማስተላለፊያ መስመሮችና ፋይበር ኦፕቲክስ ቢሮ ሥራ አስኪያጅ አቶ ህንፃ አረጋዊ እንዲህ ዓይነት ጣቢያ ጎብኝተው እንደማያውቁ ገልፀው በጉብኝቱ ከተደረገው ገለፃ ስለ ቴክኖሎጂው ግንዛቤ ማግኘታቸውን እና ጣቢያው ከሌሎቹ የተለየ ትኩረት እንደሚፈልግ መረዳታቸውን ተናግረዋል።

Scroll to Top