ሪጅኑ የፕላንት ሜንቴናንስ ሞጁል የተጠቃሚዎች ስልጠና እየሰጠ ነው

ሪጅኑ የፕላንት ሜንቴናንስ ሞጁል የተጠቃሚዎች ስልጠና እየሰጠ ነው

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ማዕከላዊ ሪጅን 3 ሥር ለሚገኙ የማከፋፈያ ጣቢያ እና ማስተላለፊያ መስመር የጥገና እና ኦፕሬሽን ባለሙያዎች የሳፕ ፕላንት ሜንቴናንስ ሞጁል የተጠቃሚዎች ስልጠና መሰጠት ተጀመረ።

የሳፕ ትግበራ ኮሚቴ አባልና አሰልጣኝ የሆኑት አቶ ወልዳይ ገ/ትንሳኤ እንደገለጹት ሥልጠናው በሪጅኑ የማከፋፈያ ጣቢያዎች እና ማስተላለፊያ መስመሮች የአሰራር ሥርዓት ለማዘመን፣ ጠንካራ የሀብት ቁጥጥር ሥርዓት ለመዘርጋት፣ ወጭ ለመቀነስ እና ሥራን ለማቀላጠፍ አስተዋፅኦው ከፍ ያለ ነው።

የፕላንት ሜንቴናንስ ሞጁል የማስተላለፊያና ማከፋፈያ ጣቢያዎችን ንብረቶች የሚመዘግብ ከመሆኑም ባሻገር የጥገና ሥራዎችን በዕቅድ ላይ ተመስርቶ ለማከናወን ፋይዳው የጎላ መሆኑን አስረድተዋል።

እንደ አቶ ወልዳይ ገለፃ የሞጁሉ መተግበር የጥገና መረጃዎችን በመሰብሰብና በመተንተን የተሻለ ውሳኔ አሰጣጥ እና ትንበያ እንዲኖር ከማስቻሉም በተጨማሪ  የጥገና ሂደቱን  ሙሉ ለሙሉ በማዘመንና በማቀላጠፍ በኩል ጉልህ ሚና ይጫወታል።

ሥልጠናው የማከፋፈያ ጣቢያዎች እና ማስተላለፊያ መስመሮችን ንብረቶች አያያዝና አጠቃቀም ለመከታተልና አስተማማኝነታቸውን ለማረጋገጥ ያስችላል፡፡

በሪጅኑ መደበኛ የፍተሻ እና የጥገና ሥራዎችን  ለመከታተልና የቁጥጥር ሥርዓቱን ለማዘመን እንዲሁም  የኃይል መቆራረጥን ለመቀነስ እንደሚረዳ አቶ ወልዳይ አብራርተዋል።

ሥልጠናው በጥገና አሰራር ሥርዓት፣ በመለዋወጫ ዕቃዎች አቅርቦት፣ አስተዳደር እና ተያያዥ ርዕሰ ጉዳዮች የሚያተኩር ሲሆን በሪጀኑ በሚተዳደሩ 20 ማከፋፋያ ጣቢያዎች ውስጥ  ለሚገኙ  ለጥገና  እና ለኦፕሬሽን ባለሙያዎች በአንድ  ወር ቆይታዎች በአራት ዙር እንደሚሰጥ አመልክተዋል፡፡

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top