ሥራ አመራር ቦርዱ ከተቋሙ ሥራ መሪዎችና ሠራተኞች ጋር ውይይት እያደረገ ነው፤

ሥራ አመራር ቦርዱ ከተቋሙ ሥራ መሪዎችና ሠራተኞች ጋር ውይይት እያደረገ ነው፤

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ አመራር ቦርድ ከተቋሙ የሥራ መሪዎች እና ሠራተኞች ጋር በተቋሙ የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም እና በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ውይይት እያደረገ ነው።

‎በውይይቱን ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ እንደገለጹት ተቋሙ ለሀገር እድገትና ሁለንተናዊ ብልጽግና ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

‎የ2017 በጀት ዓመት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ለምርቃት ዝግጁ ማድረግን ጨምሮ በተቋሙ ድርብርብ ድሎች የተመዘገቡበት ነበር ብለዋል።

‎ለዚህም የቦርድ ድጋፍና ክትትል እንዲሁም የተቋሙ ሠራተኛና አመራር ያላሳለሰ ጥረት ከፍተኛ ሚና መጫወቱ ገልጸዋል።

‎የውይይት መድረኩ የ2017 በጀት እቅድ አፈጻጸምን በመገምገም በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ሠራተኛው የጋራ ግንዛቤ ኖሮት ለተሻለ ለውጥ እንዲተጋ ለማድረግ ያለመ ነው ብለዋል።

‎በመድረኩ የተቋሙ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ በተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጅነር አሸብር ባልቻ እየቀረበ ነው።

‎በቀረበው ዕቅድና ሪፖርት ላይ በሠራተኛው ውይይት እንደሚደረግበትና የሥራ አመራር ቦርዱም ቀጣይ የሥራ አቅጣጫ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top