ምክር ቤቱ ለኃይል ዘርፍ ሪፎርም ኢንቨስትመንትና ማዘመኛ የሚውል 145 ሚሊዮን ዶላር በላይ የብድር ሥምምነት አጸደቀ

ምክር ቤቱ ለኃይል ዘርፍ ሪፎርም ኢንቨስትመንትና ማዘመኛ የሚውል 145 ሚሊዮን ዶላር በላይ የብድር ሥምምነት አጸደቀ

የኢፌዴሪ 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለኃይል ዘርፍ ሪፎርም ኢንቨስትመንትና ማዘመኛ የሚውል 145 ሚሊዮን ዶላር በላይ የብድር ሥምምነት አጸደቀ።

ምክር ቤቱ በ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባው በኢፌዴሪ መንግሥት እና በዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር መካከል ለኃይል ዘርፍ ሪፎርም ኢንቨስትመንትና ማዘመኛ ምዕራፍ አንድ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል የ145 ነጥብ 8 ሚሊዮን ዶላር የብድር ሥምምነት ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል።

በምክር ቤቱ የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር የተከበሩ አቶ ፍቃዱ ተሰማ ባቀረቡት ማብራሪያ እንደገለጹት የብድሩ ዓላማ የአዲስ አበባን የኃይል ማስተላለፊያ መረብ ለማጠናከር፣ አዳዲስ የኃይል ጣቢያዎችን ለመገንባትና ነባሮቹን ለማሻሻል እንዲሁም የመሬት ውስጥ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችን መዘርጋት የሚያስችል ነው።

የብድር ሥምምነቱ ኢትዮጵያ ለምታስተናግደው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP 32) አስተማማኝና ዘመናዊ የኃይል አቅርቦትን ለማረጋገጥ ሚናው የጎላ መሆኑን አብራርተዋል።

ብድሩ የ6 ዓመት የእፎይታ ጊዜን ጨምሮ በ31 ዓመታት ውስጥ ተከፍሎ የሚጠናቀቅ መሆኑም ጠቁመዋል።

ምክር ቤቱ የብድር ሥምምነቱን በሙሉ ድምፅ ማፅደቁን ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top