በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የበቆጂ ባለ 230/33 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ለደንበኞች አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን የፕሮጀክቱ ሳይት ሥራ አስኪያጅ ገለጹ፡፡
ሥራ አሰኪያጁ አቶ እንዳልካቸው ጃምቦ እንደገለጹት በማከፋፈፈያ ጣቢው የፍተሻ እና የሙከራ ሥራዎች ላለፉት ሦስት ወራት ሲከናወኑ ቆይተዋል።
የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያውን ከመልካ ዋከና ወደ ቆቃ ከሚሄደው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የማስተላለፊያ መስመር ጋር በማገናኘት የፍተሻና የሙከራ ሥራዎች ሙሉ በሙሉ መጠናቀቃቸውን ተናግረዋል፡፡
የፍተሻና የሙከራ ሥራው መጠናቀቁን ተከትሎ አስር ባለ 33 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመሮች ለደንበኞች አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መደረጋቸውን አስታውቀዋል፡፡
የማከፋፈያ ጣቢያው ለበቆጂና እና በ120 ኪሎ ሜትር ዙሪያ መለስ ውስጥ ለሚገኙ ከተሞች እና ወረዳዎች አስተማማኝ የኃይል ለማቅረብና የኢንቨስትመንት ፍሰት ለማፋጠን እንደሚያግዝ ጠቁመዋል፡፡
የማከፋፈያ ጣቢያው ግንባታ በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ በተቋሙ የራስ ኃይል ግንባታ መምሪያ ላለፉት አስራ ዘጠኝ ወራት ሲከናወን ቆይቷል፡፡
? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”


