ማመንጫ ጣቢያው  ከዕቅድ በላይ ኃይል ማምረት ችሏል

ማመንጫ ጣቢያው  ከዕቅድ በላይ ኃይል ማምረት ችሏል

በኢትዮዽያ ኤሌክትሪክ ኃይል ግልገል ጊቤ አንድ የውሃ ማመንጫ ጣቢያ  መንፈቀ ዓመት ከዕቅድ በላይ ኃይል ማምረቱን የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ አቶ ደሳለኝ  ንጉሳ   ገለፁ።

ሥራ አስኪያጁ   እንደገለፁት ጣቢያው  ባለፉት ስድስት ወራት 572,855,721 ኪሎ ዋት ስዓት  ኃይል ለማምረት አቅዶ 587,411,770 ኪሎ ዋት ስዓት በማምረት የዕቅዱን 102.57 በመቶ ማሳካት ችሏል ፡፡

የጣቢያው የማመንጨት አፈፃፀም ከፍ ሊል የቻለው የቅድመ ጥገና  ስራዎች  በተያዘላቸው ዕቅድ መሰረት በመከናወናቸውና  ለኦፕሬንሽን ስራዎው አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት በመደረጉ ሦስቱም ዩኒቶች በሙሉ አቅማቸው እየሰሩ በመሆኑ እደሆነ  አቶ ደሳለኝ ገልፀዋል።

አመታዊ ዕቅዱን ከማሳካት አንፃር ግዱቡ በቂ ወሃ መያዙንም  ሥራአስኪያጁ አክለው ገልፀዋል።

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top