በኢትዮዽያ ኤሌክትሪክ ኃይል የፊንጫ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ባለፉት ሶስት ወራት ከዕቅድ በላይ ኃይል ማምረቱን የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ አስታወቁ።
ሥራ አስኪያጁ አቶ ታደሠ ፈቃዱ እንዳስታወቁት ጣቢያው በሩብ በጀት ዓመቱ 169 ሜጋ ዋት ስዓት ኃይል ለማምረት አቅዶ 218 ሜጋ ዋት ስዓት በማምረት የዕቅዱን 128 ነጥብ 57 በመቶ ማሳካት ችሏል ፡፡
የጣቢያው የማመንጨት አፈፃፀም ከፍ ሊል የቻለው በኦፕቲካል ሊንክ ሞጁል ብልሽት ምክንያት ቆሞ የነበረው አንድ ዩኒት ወደ ስራው በመመለሱ ነው ብለዋል።
የጣቢያውን ኃይል የማምረት አቅም የሚያሳድጉ የጥገና ሥራዎች በተያዘላቸው ዕቅድ መሰረት መሰራታቸውም ለአፈጻጸሙ ከፍ ማለት የጎላ ድርሻ ማበርከቱን ጠቁመዋል።
የመለዋወጫ ዕቃዎችን ሞዲፋይ አድርጎ በራስ ዓቅም በመጠገን ማሽኖች እንዳይቆሙ መደረጉ በሩብ ዓመቱ በጥንካሬ ሊነሳ የሚችል መሆኑን ተናግረዋል።
? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

