መምሪያው የተቋሙን የአሠራር ስርዓት ለማዘመን እየሰራ መሆኑን ገለፀ

መምሪያው የተቋሙን የአሠራር ስርዓት ለማዘመን እየሰራ መሆኑን ገለፀ

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የፕሮሰስ፣ ፖሊሲና የለውጥ ሥራ አመራር መምሪያ ቀልጣፍ እና ውጤትን መሠረት ያደረገ የአሠራር ስርዓት ለመዘርጋት የሚያስችሉ ተግባራት እያከናወነ መሆኑን አስታወቀ።

የመምሪያው ዳይሬክተር አቶ አንዷለም ኪዳኔ እንደተናገሩት የአሰራርና የዶክመንቴሽን ስርዓቶችን በማዕከል ለማደራጀት፣ ደህንነታችውን ለመጠበቅና ለተጠቃሚዎች ምቹ ለማድረግ የሚያስችል ሲስተም የማበልጸግ ስራ ተከናውኗል።

የተቋሙን የመፈፀም አቅም የሚያጎለብቱ የፖሊሲ ዝግጅት፣ መመሪያ፥ ማጣቀሻ ሰነዶች እና ቴምፕሌቶች ተዘጋጅተው ወደ ስራ መገባቱን ዳይሬክተሩ አብራርተዋል።

በተጨማሪም ከተለያዩ የስራ ክፍሎች የተውጣጡ የፖሊሲ ዝግጅት ቡድኖች ስልጠና ወስደው የፖሊሲ ቀረፃ ለማከናወን በዝግጅት ምዕራፍ ላይ እንደሚገኙም ነው የገለፁት።

የተቋማዊ ባህል ማኑዋል የተዘጋጀ መሆኑን እና በተቋም ደረጃ ያለውን የሥራ ባህል ለማጎልበት የሚረዳ ሥልጠና ለ202 የተቋሙ አመራሮች መሰጠቱን ተናግረዋል።

እንደ አቶ አንዷለም ገለፃ ውጤታማ የሰዓት አጠቃቀምን ሥርዓት ለመዘርጋት ከተቋሙ የኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ጋር በመተባበር ለሠራተኞች ተከታታይ ክፍሎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ተከናውኗል።

ከብክነት የፀዳ እና ምቹ የአሠራር ስርዓት ለመዘርጋት በማዕከላዊ 2 ሪጅን በሚገኙት ኮዬ አቦ፣ ገላን፣ቢሾፍቱ 1 እና 2 የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች የካይዘን ትግበራ መጀመሩን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

ይህንን አሠራር ይበልጥ ለማስፋት በተከዜ፣በቆቃ፣በአዋሽ 1 እና 2፣ በአሸጎዳ፣ በአዳማ 1 እና 2 ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ስልጠና መሰጠቱንም አብራርተዋል።

የዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት የመምሪያውን የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት አፈፃፀም ገምግሟል።

💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top