መምሪያው በኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ደህንነትና ጥበቃ የተከናወኑ ሥራዎችን እየገመገመ ነው

መምሪያው በኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ደህንነትና ጥበቃ የተከናወኑ ሥራዎችን እየገመገመ ነው

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተቋም ደህንነትና አስተዳደራዊ ጉዳዮች መምሪያ የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በሀዋሳ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል።

የመምሪያው ዳይሬክተር አቶ ከሊል ሺፋ እንደገለጹት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማው በተቋሙ የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ላይ የሚፈጸሙ ሥርቆቶችን በመከላከል ረገድ ባለፈው ዘጠኝ ወራት በሪጅኖች የተከናወኑ ሥራዎችን፣ የተመዘገቡ ስኬቶችን እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች በዝርዝር ይመለከታል።

የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማው በተቋሙ ንብረት ላይ የሚፈፀሙ ስርቆቶችን ለመከላከል በተከናወኑ ሥራዎች የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገቡ ሪጅኖችን ተሞክሮ በማስፋት ልምድ የሚወሰድበት መሆኑንም ገልጸዋል።

ተቋሙ በሁሉም ሪጅኖች የመደባቸው ከመከላከያ ሠራዊት የተውጣጡ የቀድሞ ከፍተኛ የመከላከያ መኮንኖች ከፌደራልና ከአካባቢው መስተዳደር እና የጸጥታ አካላት ጋር የነበራቸው ቅንጅታዊ አሰራር ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ቀርቦ እንደሚገመገም ገልፀዋል።

በግምገማው የሁሉም ሪጅኖች የሥራ ኃላፊዎችና በሥራው ላይ በቀጥታ የተሳተፉ የመከላከያ ሠራዊት የቀድሞ ከፍተኛ መኮንኖች፣ ከፌደራልና ከክልል መስተዳደሮች የተውጣጡ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የጸጥታ አካላት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ታድመዋል።

ለሦስት ቀናት በሚቆየው ግምገማ ስርቆትን በመከላከል የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ደህንነትን ለማረጋገጥ በተዘረጋው አዲስ አሰራር ሪጅኖች ያስመዘገቧቸው ለውጦችን ገምግሞ የቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ እንዲሁም ስርቆት በተደጋጋሚ በሚፈጸምባቸው የደቡብ አንድ ሪጅን የተመረጡ ቦታዎች የመስክ ምልከታ በማካሄድ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

Scroll to Top