በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚፈልገውን የኃይል አቅርቦት ለማሟላት የሚያስችል በቂ ኃይል መኖሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለፁ፡፡
ጠቅላይ ሚንስትሩ የፌደራል መንግስት የ2017 የመጀመሪያ ግማሽ በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸምን አስመልክቶ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ሲሰጡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለፁት በፋብሪካዎችና ኢንዱስትሪዎች በተደረገ ጥናት ቀደም ሲል ሲነሳ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ችግር ሙሉ በሙሉ ተፈቷል፡፡
እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ በበጀት ዓመቱ 8 ወራት ለኢንዱስትሪ ሴክተሩ የቀረበው የኤሌክትሪክ ኃይል ምርት 50 በመቶ ዕድገት ሲያሳይ በሀገር ደረጃ ደግሞ 47 በመቶ የኃይል ፍላጎት ዕድገት ተመዝግቧል፡፡
የሚታየው የፍላጎት ዕድገት ከፍተኛ ዝግጅት እንደሚጠይቅ ያሳየ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ታሳቢ ያደረገ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ግንባታ አስፈላጊ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”
