ለተቋሙ የሥራ ኃላፊዎችና  ሠራተኞች  የግዥ አፈጻጸም ሥልጠና  እየተሰጠ ነው

ለተቋሙ የሥራ ኃላፊዎችና  ሠራተኞች  የግዥ አፈጻጸም ሥልጠና  እየተሰጠ ነው

በኢትዮጵያ  ኤሌክትሪክ ኃይል ከሁሉም የሥራ ክፍሎች ለተውጣጡ የሥራ ኃላፊዎች እና  ባለሙያዎች አዲስ በወጣው የመንግስት የልማት ድርጅቶች የግዢ አዋጅና መመሪያ አፈፃፀም ዙሪያ ሥልጠና በመሰጠት ላይ ነው።

የተቋሙ የግዥና ሎጀስቲክስ ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ጽዮን ብርሃኑ እንደገለፁት የግዢ አፈፃፀም ሂደትን ማወቅ የግዥ ፈጻሚው ክፍል ብቻ ሳይሆን ግዥ እንዲፈጸምለት ጥያቄ ያቀረበው የሥራ ክፍል ሥራ መሆን ስላለበት ሥልጠናው ከተቋሙ የግዢ ባለሙያዎች በተጨማሪ ሌሎች የሥራ ክፍሎችን ጭምር ማካተቱን ገልፀዋል፡፡

ስለሆነም ስልጠናው የሚቀርቡ የግዢ ጥያቄዎች በጊዜና በጥራት ህግን ተከትለው ተፈጻሚ እንዲሆኑ እንደሚያግዝ ገልፀዋል፡፡

በስልጠናው  ላይ ተሳታፊ የሆኑት በተቋሙ የጤናና ሴፍቲ ሥራ አሰኪያጅ አቶ ኮርሳ ታሬሳ በበኩላቸው ሥልጠናው በግዢ ሂደት ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመቅረፍ ግዢዎችን በአግባቡ ለመፈፀም የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

እንደ ሥራ አስኪያጇ ገለጻ እየተሰጠ የሚገኘው ሥልጠና በተቋሙ ግዢና ሎጀስቲክስ  መምሪያ እንዲሁም በመንግስት ሀብት አስተዳደር እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ በጋራ መዘጋጀቱ ውጤቱን የላቀና ከፍተቶችን የሚሞላ ሥልጠና ያደርገዋል ብለዋል፡፡

በተቋሙ የሚፈጸሙ የግዢ ሂደቶች ወጥነት ያለው እና ሃገራዊ የግዢ ስርዓትን በመከተል ተፈጻሚ እንዲሆኑ የሚያስችል እውቀት ከስልጠናው እያገኙ መሆኑን የገለጹት ደግሞ ከልማትና ስልጠና ማዕከል ተሳታፊ የሆኑት ወ/ሮ የምስራች መኮንን ናቸው፡፡

የሠራተኛ ማኅበር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኃይሉ ወልዴ በበኩላቸው ሥልጠናው በግዢ አፈፃፀም ሂደት ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን አሟልቶ የተሻለና ህግን የተከተለ አሰራር ለመዘርጋት እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡

💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top