
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ጋር በመተባበር በአመራር እና የተቋም ባህል ግንባታ ላይ ያተኮረ የሦስት ቀን ሥልጠና ለተቋሙ የሥራ ኃላፊዎች መስጠት ጀመሯል።
የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተወካይና የጀነሬሽን ቢዝነስ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ኤፍሬም ወልደ ኪዳን በስልጠናው መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለሀገሪቷ እና ለቀጣናው አስተማማኝ ኃይል በማቅረብ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያበረከተ ነው።
አመራሩ የተሰጠውን ኃላፊነት በብቃት እንዲወጣ እና የመፈጸም አቅሙ እንዲጎለብት ሥልጠና ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።
ስለሆነም አመራሩ ሥልጠናውን በንቃት በመከታተል የተቋሙን ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ለማሳካት የሚያስችል አቅም እንዲገነባ አሳስበዋል።
ሥልጠናው ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዛዲግ አብርሃ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እና የመሪነት ሚና ላይ ያተኮረ ሥልጠና በመስጠት ላይ ናቸው።
💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”



