የኢትዮ-ኤሌክትሪክ ታዳጊ እግር ኳስ ቡድን ሻምፒዮን ሆነ

የኢትዮ-ኤሌክትሪክ ታዳጊ እግር ኳስ ቡድን ሻምፒዮን ሆነ

የኢትዮ-ኤሌክትሪክ ከ17 ዓመት በታች ታዳጊ እግር ኳስ ቡድን በሐዋሳ ከተማ በተካሄደው የኢትዮጵያ ሻምፒዮና አሸናፊ በመሆን የዋንጫ እና የወርቅ ሜዳሊያ ተሸልሟል።

በዛሬው ዕለት ሐዋሳ ስታዲየም በተካሄደው የፍፃሜ ጨዋታ የኢትዮ-ኤሌክትሪክ ታዳጊ ቡድን የሲዳማ ክልል አቻውን በማሸነፍ የውድድሩ ሻምፒዮን ሆኗል።

ሁለቱ ቡድኖች በመደበኛው 90 ደቂቃ ባዶ ለባዶ የተለያዩ ሲሆን አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠው የፍፁም ቅጣት ምት የኢትዮ-ኤሌክትሪክ ታዳጊ ቡድን 4 ለ 3 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የኢትዮ ኤሌክትሪክ ታዳጊ ተጫዋች ተመስገን ማናዬ በኮከብ ተጫዋችነት የተመረጠ ሲሆን የቡድን አጋሩ ሙባረክ አረቦ ደግሞ ኮከብ ግብ አግቢ በመሆን ተሸልሟል።

በተጨማሪም የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ሙሉጌታ በዳዳ ኮከብ አሰልጣኝ እንዲሁም ተስፈኛው ታዳጊ ብሩክ ዘላለም ኮከብ ግብ ጠባቂ በመሆን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ከአቶ ባህሩ ጥላሁን ሽልማታቸውን ተረክበዋል።

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top