ኢትዮ-ኤሌክትሪክ በፕሪሚየር ሊጉ ባደረገው የመጀመሪያ ጨዋታ ሽንፈት ገጥሞታል

ኢትዮ-ኤሌክትሪክ በፕሪሚየር ሊጉ ባደረገው የመጀመሪያ ጨዋታ ሽንፈት ገጥሞታል

በድሬዳዋ ከተማ በተጀመረው የዘንድሮ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን ከወላይታ ዲቻ ጋር ባካሄደው ጨዋታ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት ተረቷል።

በዛሬው ዕለት ከቀኑ 10 ሰዓት በተከናወነው በዚህ ጨዋታ ኳስን ተቆጣጥሮ በመጫወት እና ወደፊት በማጥቃት ረገድ ወላይታ ዲቻ የተሻለ ነበር።

በአንፃሩ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ አልፎ አልፎ በመልሶ ማጥቃት ካደረገው እንቅስቃሴ በስተቀር በመከላከል ላይ የተመሠረተ አጨዋወት ነበር ተግባራዊ ያደረገው።

የወላይታ ዲቻን የማሸነፊያ ጎሎች ተስፋዬ መላኩ፣ ካርሎስ ዳምጠው  እና ጌታሁን ባፍ በራሱ ግብ ላይ ሲያስቆጥር  ኢትዮ ኤሌክትሪክን ከሽንፈት ያልታደጉትን ጎሎች እዮብ ገ/ማርያም እና አቤል ሀብታሙ  ከመረብ አሳርፈዋል።

ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ባለፈው ዓመት በተከናወነው የከፍተኛ ሊግ ውድድር አንደኛ በመሆን ወደ ፕሪሚየር ሊጉ መመለሱ ይታወሳል።

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top