ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ፋሲል ከነማን አሸነፈ

ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ፋሲል ከነማን አሸነፈ

ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ፋሲል ከነማን አሸነፈ በ7ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ፋሲል ከነማን ገጥሞ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሁለተኛ ተከታታይ ድሉን አስመዝግቧል።

ሁለቱ ቡድኖች በድሬዳዋ ስቴዲየም ዛሬ ባከናወኑት ጨዋታ አቤል ሀብታሙ፣ ናትናኤል ገ/ጊዮርጊስ እና ያሬድ የማነ ለኢትዮ-ኤሌክትሪክ ሶስቱን የማሸነፊያ ጎሎች አስቆጥረዋል።

ፋሲል ከነማን ከሽንፈት ያልታደጉትን ሁለት ጎሎች አንጋፋው አጥቂ ጌታነህ ከበደ ከመረብ አሳርፏል።

ብርቱ ፉክክር በታየበት የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ በመስመር ላይ የተመሰረተ የማጥቃት እንቅስቃሴ ሲከተል ፋሲል ከነማ በአንፃሩ ኳስን በመቆጣጠር የጨዋታ ብልጫ ለመውሰድ ቢሞክርም ሳይሳካለት ቀርቷል።

ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ በ12 ነጥብ በሊጉ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top