ኢትዮ-ኤሌክትሪክ የዋንጫ አሸናፊ ሆኗል

ኢትዮ-ኤሌክትሪክ የዋንጫ አሸናፊ ሆኗል

በቢሾፍቱ ከተማ በተካሄደው 11ኛው የኢትዮጵያ የ30 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር ኢትዮ-ኤሌክትሪክ በሁለቱም ፆታ አሸናፊ ሆኗል።

በወንዶች በተካሄደው ውድድር የኢትዮ-ኤሌክትሪክ አትሌት ኃይለ ማርያም ኪሮስ 1ኛ በመውጣት የወርቅ ተሸላሚ ሲሆን የቡድን አጋሩ አትሌት ባየልኝ ተሻገር ውድድሩን በሶስተኛነት አጠናቋል፡፡

በተመሳሳይ የሴቶች የሩጫ ውድድር አትሌት ጽጌ ኃይለ ሥላሴ 2ኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ ባለቤት ሆናለች፡፡

ኢትዮ-ኤሌክትሪክ በአጠቃላይ ነጥብ አንደኛ በመሆን የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶለታል።

በዚህ ውድድር ከሶስት ክልሎች፣ከአንድ ከተማ አስተዳደር እና ከ15 ክለቦች የተውጣጡ 522 አትሌቶች ተሳትፊ ሆነዋል።

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top