ድሬዳዋ ከተማ እየተካሄደ ባለው የኢትዮጵያ የወንዶች ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ከድሬዳዋ ከነማ ጋር ነጥብ ተጋርቷል።
ትናንት ምሽት አንድ ሰዓት የተከናወነው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ያለምንም ግብ ተጠናቋል።


ግብ የሚሆኑ ኳሶችን በተደጋጋሚ ሙከራ በማድረግ ድሬዳዋ ከነማ የተሻለ ሲሆን ኢትዮ-ኤሌክትሪክ በአንፃሩ በመልሶ ማጥቃት ጎል ለማግኘት ጥረት ሲያደርግ ተስተውሏል።
የኢትዮ-ኤሌክትሪክ ግብ ጠባቂ ኢድሪሱ አብዱላሂ በርካታ ጎል ሊሆኑ የሚችሉ ኳሶችን በማዳን ክለቡን ታድጓል።
ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ በ14 ነጥብ መቻልን ተከትሎ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ በጊዜያዊነት በሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
በ10ኛ ሳምንት መርሃግብር ኢትዮ-ኤሌክትሪክ በመጪው ህዳር 27 ቀን 2017 ዓ.ም ከስሁል ሽረ ጋር የሚጫወት ይሆናል።
? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”



