ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ተሸንፏል

ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ተሸንፏል

በአበበ ቢቂላ ስቴዲየም ዛሬ በተከናወነ የ6ኛ ሳምንት የሴቶች ፕሪሚዬር ሊግ ጨዋታ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ ለባዶ ተረቷል።

የንግድ ባንክን ብቸኛ የማሸነፊያ ጎል ብርቱካን ገ/ክርስቶስ በ27ኛው ደቂቃ አስቆጥራለች።

በጨዋታ የበላይነት የነበረው ኢትዮ-ኤሌክትሪክ በርካታ ግብ ሊሆኑ የሚችሉ ኳሶችን ቢያገኝም በሚያስቆጭ ሁኔታ ዕድሎቹን አምክኗል።

በአንፃሩ ንግድ ባንኮች ያገኘውን ብቸኛ ዕድል ወደ ጎል በመቀየር ማሸነፍ ችሏል።

በ7ኛ ሳምንት መርሃግብር ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ከአዳማ ከነማ ጋር ህዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም ይጫወታል።
  
? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top