በ6ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሜርሊግ ጨዋታ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ፡ ሐዋሳ ከተማን 2 ለ 1 በማሸነፍ ሁለተኛ ድሉን ማስመዝገብ ችሏል።
ትናንት ምሽት አንድ ሰዓት በተከናወነው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በ11ኛው ደቂቃ ዓሊ ሱለይማን ባስቆጠራት ጎል ሐዋሳ ከተማ ቀዳሚ መሆን ችሏል።
የሐዋሳው በረከት ሳሙኤል በ43ኛው ደቂቃ በራሱ ግብ ላይ ባስቆጠራት ጎል አቻ መሆን የቻለው ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ኢዮብ ገ/ማርያም በ89ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ሁለተኛ ጎል ድል ተቀዳጅቷል።
ተመጣጣኝ የጨዋታ ፉክክር በታየበት የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በርካታ ግብ የሚሆኑ ኳሶች መክነዋል።
ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ በፕሪሜርሊጉ አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”





