ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ዳግም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን መቀላቀሉን አረጋገጠ

ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ዳግም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን መቀላቀሉን አረጋገጠ

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ትናንት በተከናወነው መርሐ ግብር ኦሮሚያ ፖሊስ ነጥብ መጣሉን ተከትሎ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ አምስት ጨዋታ እየቀረው ወደ ፕሪሚየር ሊግ ማደጉን አረጋግጧል።

በዘንድሮ የውድድር ዘመን ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ውድድሩ ከጀመረበት ዕለት ጀምሮ ሊጉን በመምራት እና አምስት ጨዋታ እየቀረው ሻምፒዮናነቱን በማረጋገጡ አዲስ ታሪክ መፃፍ ችሏል።

በ1953 ዓ.ም የተመሠረተው አንጋፋው ኢትዮ-ኤሌክትሪክ በስፖርቱ ዘርፍ በርካታ እንቁ ተጫዋቾች ለሀገር አበርክቷል።

በተገኘው ድል መላው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ ለተቋሙ የሥራ አመራሮች እና ሠራተኞች እንኳን ደስ አለን የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።

በስፓርቱ የተገኘውን ስኬት ተቋማዊ ዕቅዶችን በማሳካት እንዲደግመው ጥሪ አቅርበዋል።

Scroll to Top